Love, Simon

Love, Simon (እንግሊዝኛ)(በአማርኛ "ከፍቅር ጋር፣ ሳይመን") 2018 እ.አ.አ የተለቀቀ በBecky Albertalli በተጻፈው Simon vs. the Homo Sapiens Agenda በተባለው መጽሐፍ መሰረት በGreg Berlanti የተዘጋጀ አሜሪካዊ የፍቅርና ወጣት ኮሜዲ-ድራማ ፊልም ነው። ዋና ዋና ተዋናዮቹ Nick Robinson, Josh Duhamel እና Jennifer Garner ናቸው። የፊልሙ ጭብጥ የሚያጠነጥነው ሳይመን ስፒየር (Simon Spier) በተባለ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ ላይ ነው። ሳይመን እራሱን ይፋ ያላወጣ የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪ ሲሆን ይህም እንዳይታወቀብት ሚስጥሩን ከቤተሰቡና ጓደኞቹ እንዲሁም ማንነቱን ለትምሕርት ቤት ሊያጋልጥው ካስፈራራው ሰው ጋር የሚያደርገውን ትግል ያሳያል። በተጨማሪም በበይነ መረብ ከተዋወቀው እና ፍቅር ካስያዘው ነገር ግን ማንነቱን የማያውቀውን የክፍል ጓደኛው ማን እንደሆን ለማወቅ የሚያደርገውንም ጥረት ያሳያል።

Love, Simon መጀመሪያ የታየው ፌብሪወሪ 27፣ 2018 እ.አ.አ በMardi Gras Film Festival ሲሆን በይፋ የተለቀቀው በዩናይትድ ስቴትስ ማርች 16 2018 እ.አ.አ ነው። የፊልም ተቺዎች በበኩላቸው ፊልሙ ባሉት "ደማቅ የፍቅር ስሜት፣ ለየት ለየት ያለ የተዋናዮች ቡድንና አብዮታዊ መደበኛነት" አሞግሰውታል። በተጨማሪም ፊልሙን "አስደሳችና ልብ የሚነካ" መሆኑን ገለጸዋል። በስመ ጥር የሆሊውድ ስቱዲዮ የተሰራ የመጀመሪያው በተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪ ወጣት የፍቅር ሕይወት ታሪክ ላይ ያተኮረው ፊልም በዓለም ዙሪያ $65 ሚሊዮን ብር ገቢ አስገኝቷል።


From Wikipedia, the free encyclopedia · View on Wikipedia

Developed by Tubidy